Dagi Tilahun Enes Alegn Скачать
Текст песни
አንደበቴ አይፈታም ሥራ
ለምሥጋና ስለ ተሰራ
የልቤ ሀሳብ የአፌ ቃል
አማረልኝ ዕልልታ ይዟል
አንደበቴ አይፈታም ሥራ
ለምሥጋና ስለ ተሰራ
የልቤ ሀሳብ የአፌ ቃል
አማረልኝ ዕልልታ ይዟል
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
ሁሉም ነገር አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
የሚታየው አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
የሚሰማው አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ክብር ዝና አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
አሃ አሃ አንተን ፈልጌ አሃ አሃ ውስጤማ ናፍቆ
አሃ አሃ ፍቅርህ ገባብኝ አሃ አሃ በልቤ ዘልቆ
አሃ አሃ ይኸው ሽብሸባ አሃ አሃ ለስምህ ጉዳይ
አሃ አሃ የእኔስ እልልታ አሃ አሃ ይሂድ ወደላይ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ
አንተ በሰራኸው አልወስድም ምሥጋና
ልቤን ከፈትኩ እንጂ ምን አደረኩና
አንተ በሰራኸው አልወስድም ምሥጋና
እንኳን ተቀንሶ መቼ ይበቃና
ይኸው ይኸው ዕልልታው ይኸው
(ይኸው ይኸው ዕልልታው ይኸው)
ይኸው ይኸው ሽብሸባው ይኸው
(ይኸው ይኸው ሽብሸባው ይኸው)
ይኸው ይኸው እልልታው ይኸው
ይኸው ይኸው አምልኮው ይኸው
ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና
ባለቤቱ የዕልልታ ይኸውልህ ይኸው ጌታ
ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና
ባለቤቱ የዕልልታ ይገባሀል የእኔ ጌታ
መሻቴ የእኔማ ደስታ ሲያውድህ የአምልኮ ሽታ
አላማ የመፈጠሬ ለዚህ ነው ላምልክ አብሬ
ቅሬታ የለም ትካዜ ምስጋናን ባሰብኩኝ ጊዜ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
አንደበቴ አይፈታም ሥራ
ለምሥጋና ስለ ተሰራ
የልቤ ሀሳብ የአፌ ቃል
አማረልኝ ዕልልታ ይዟል
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
ሁሉም ነገር አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ገንዘብ ንብረት አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ስልጣን ሹመት አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ዘውዱ ንግሱ አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ
ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና
ባለቤቱ የዕልልታ ይኸውልህ ይኸው ጌታ
ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና
ባለቤቱ የዕልልታ ይገባሀል የእኔ ጌታ
Треки от исполнителя