Madingo Afework Tzita Скачать
Текст песни
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመዉ
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመዉ
ትርጉሙ ምንድነው ምንድነው
ምንድነው ሰው ማሰብ ምንድነው ትዝታ
ባክህ ተዉ የማይሉት የሁሉም ሰዉ ጌታ
ይሃዉ ሰው ይኖራል በትዝታ ሰበብ(፪)
የሃሊት ሲጋልብ ትናንት በማሰብ
ሰው እንዴት ባለፈው በትናንት ይኖራል(፪)
ዛሬን በእጁ ይዞ ለነገው መሰላል(፪)
እልል በል ትዝታ ልርሳ በሽታዬን
አትጋርደኝ ልይበት የነገን ተስፋዬን
ባይጠፋ አሻራው ትዝታ ቢነፍስም
ባለፈ አመት ዝናብ ዛሬ አይታረስም
በትዝታ ሰበብ ላለፈው ሲጨነቅ
ስንት ሰው አለፈ ከአምላክ ሳይታረቅ
እገነባለሁ ብዬ ድካሙ ቢያመኝም
ለፈረሰዉ ቤቴ ሳለቅስ አልገኝም
ያለፈን ላይቀይር በከንቱ ይለፋል(፪)
መቼም ሰው ደፋር ነው ፈጣሪን ይጋፋል
ትንሽ እልፍ ሲሉ እልፍ እየተገኘ(፪)
ድሀ ነው በልቡ ሞትን የተመኘ
ንንን ንንን ንንን
ንንን ንንን ንንን
ንንን ንንን ንንን
ንንን ንንን ንንን(፪)
ንንን ንንን ንንን(፪)
ለምን በትዝታ ኑሮዬን እገፋለሁ(፫)
ማጣትም እንዳለ ለማግኘት ጊዜ አለዉ(፪)
አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም(፫)
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም(፮)
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመዉ
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመዉ
На странице доступен трек Tzita от Madingo Afework. Слушайте онлайн или загрузите в один клик бесплатно на свое устройство.